የሙስሊሞች ጉዳይ መፅኤት አዘጋጆች ጋዜጠኛ አክመል ነጋሽ እና ጋዜጠኛ ይስሐቅ እሸቱ የሚወዷትን ሀገራቸዉን ጥለዉ ወደ ሌላ ሀገር መሰደዳቸዉን አስታወቁ:: ሁለቱ የሙስሊም ጋዜጠኞች ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በሰጡት የስልክ ቃለ መጠይቅ እንደገለፁት መንግስት ለኢትዮጲያ ሙስሊም ሲያገለግሉ የነበሩ ሰዎችን እያሳደደ ማደኑን በመቀጠሉና በሙስሊሙ ላይ የሚደርሰዉ ግፍና ስቃይ እየበዛ በመምጣቱ የሚወዷትን ሀገራቸዉን ጥለዉ መሰደዳቸዉን ገልፀዎል:: የት ሀገር እንደተሰደዱ ግን ለደህንነታቸዉ ሲሉ አለመግለፃቸዉን ከቃለ መጠይቁ ለመረዳት ተችሏል:
No comments:
Post a Comment