Saturday, 11 August 2012

ድምፃችን ይሰማ

በደሴ ከተማ የጁምአ ሰላት ለመስገድ በአረብገንዳ መስጂድ የተሰበሰቡ ንፁሀን ሙስሊሞችን ፓሊስ ለምን ቁጥራቹ ቢበዛምከመስጂዱ ቅጥር ግቢ ወጣችሁ በማለት በወሰደዉ የሀይል እርምጃ በርካታ ሴቶች እና ወንዶች መጎዳታቸዉን ምንጮች ገለፁ:: በመስጂዱ ዉስጥ ፖሊስ አግቷቸዉ የነበሩ ሙስሊሞችን ከመስጂዱ በማሶጣት በመኪና በመጫን እንደወሰዷቸዉ የተገለፀ ሲሆን የት እንደወሰዷቸዉ ግን እስካሁን ማወቅ አለመቻሉን ምንጮች አስታዉቀዎል:: የ80አመቱን የአረብ ገንዳ መስጂድ ኢማም ታላቁ አሊም ሼህ አደም ሙሳን ፓሊሶች እያንገላቱና እየሰደቡዎቸዉ ይዘዎቸዉ መሄዳቸዉን ምንጮች አስታዉቀዎል:: የመስጂዱን አስተዳደር የሆነዉን ባህረዲንንም ወስደዉ አስረዉታል:: ከምሽቱ ስድስት ሰአት ቡሀላም ፓሊስ ወደፍርቃን እና ዳዌሜዳ አራዶ መስጂድ ዘልቆ በመግባት ኢትካፍ የገቡ ሙስሊሞችን ለማወክ የሞከረ ሲሆን ሁለቱንም መስጂዶች ፈትሸዎል:: የፍርቃን መስጂድ ኢማም የሼህ መሀመድ ሀሚዲን አ/ሰመድ ታላቅ ወንድም የሆኑት ታላቁ አሊም ሼህ ሀሰን ሀሚዲን አ/ሰመድን ይዘዎቸዉ ወስደዉ አስረዎቸዎል:: በተመሳሳይም የደሴ አሬራ መስጂድ ኢማም የሆኑትን ሼህ ጀማልንም ፓሊሶች ማሰራቸዉን ለማወቅ ተችሏል :: ኢማሞቹ እስካሁን የት እንደታሰሩ ለማወቅ አልተቻለም:: አላህ ይድረስላቸዉ!!!

No comments:

Post a Comment