Friday, 10 August 2012
ድምፃችን ይሰማ
በደሴ ከተማ የጁምአ ሰላት ለምን ከመስጂዱ ዉጪ ትሰግዳላቹ በማለት የከተማዎ ፖሊስ ከሙስሊሙ ጋር አለመግባባት በመፈጠሩ የፌደራል ፖሊስ እና አድማ በታኞችን በመጥራት ሙስሊሙን መደብደባቸዉን እና ጭስ እየተኮሱ ለጁምአ ሰላት የመጣዉን ንፁሀን ሙስሊሞች መበተናቸዉን ምንጮች አስታወቁ:: ሰላም ወዳዱ የደሴ ህዝብ ፖሊስ ሆን ብሎ ረብሻ ለመፍጠር ማቀዱን ትላንት ማታ መረጃዉ ስለደረሳቸዉ ባለፈዉ ሳምንት የጁምአ ሰላት በአረብ ገንዳ መስጂድ ሲሰግዱ ህዝቡ በመብዛቱ መስጂዲ ሞልቶ አስፉልት ላይ ሰግደዉ የነበረ ሲሆን በዛሬዉ ጁምአ ግን የፖሊስን ሴራ ለማክሸፍ አስፉልት ላይ ከመስገድ በመቆጠብ በመስጂዱ ዙሪያ ባሉ የዉስጥ መንደሮች ለመስገድ በመሰብሰባቸዉ የፌደራል ፖሊስ ጭስ በመተኮስ እንደደበደባቸዉ ምንጮች አስታዉቀዎል:: በጭሱም በርካታ ንፁሀን ሙስሊም ሴቶች እራሳቸዉን ስተዉ የወደቁ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ወደ መስጂዱ አስገብተዎቸዉ የመጀመሪያ እርዳታ ሙስሊሙ እያደረገላቸዉ ይገኛል:: የፌደራል ፖሊስ ዉጪ ያለዉን ህዝብ ደብድቦ ካባረረ ቡሀላ መስጂዱን በመዝጋት በመስጂዱ ወስጥ ያሉ ሙስሊሞች እንዳይወጡ ማገዳቸዉ ተገልፆል:: በመስጂዱ ዉስጥ ያሉ ሙስሊሞችም ሴቶችን እንዲወጡ ያደረጉ ሲሆን ወንዶቹ ግን በፌደራል ፖሊስ ታግተዉ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አስታዉቀዎል:: በአረብ ገንዳ የታገቱት ሙስሊሞች በአሁኑ ሰአት ተረጋግተዉ በመስጂዱ ዉስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል:: አሁን ያለዉ ሁኔታ በአ.አ በታላቁ አንዎር መስጂድ የተፈፀመዉን ድርጊት ለመድገም ያሰቡ ይመስላል:: በአንድ የደሴ ከተማ ፖሊስ ትንኮሳ በተፈጠረ አለመግባባት ለጁምአ ሰላት የተሰበሰቡ ንፁሀን ሙስሊሞች ለድብደባ ዳርጏቸዎል:: አላህ ይረዳቸዉ ዘንድ ዱአ አድርጉላቸዉ:: ያለዉን አዲስ ነገር በፍጥነት ለአንባቢያን እንደምንዘግብላቹ እናሳዉቃለን!!
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment