Sunday, 12 August 2012

ድምፃችን ይሰማ


ድምፃችን ይሰማ
በቡራዩ አካባቢ መንግስት በግዳጅ የሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ተቃዉማቹ ሰልፍ ዉጡ በማለት የአካባቢዉን ሙስሊም ነዎሪዎች አስገድዶ የነበረ ሲሆን የአካባቢዉ ሙስሊሞች ግን በመንግስት ማስፈራሪያ ሳይበገሩ ለዲናቸዉ ያላቸዉን ታማኝነት ያረጋገጡ ሲሆን በሰልፍ ላይ በየቤቱ በመግባት ያገኙትን ሴትና ህፃናት እያስገደዱ ማሶጣታቸዉን ለማወቅ ተችሏል:: የአካባቢዉ ሙስሊሞች በሰልፍ ላይ ባለመገኘታቸዉ መንግስት ከሌላ አካባቢዎች በመኪና ሰዎችን አበል እየከፈለ ያስመጣ ሲሆን የቡራዩ አካባቢ ያገኛቸዉን ክርስቲያኖች ኑ አክራሪነትን ተቃወሙ በማለት በሰልፍ ላይ እንዲካፈሉ ማድረጋቸዉን ምንጮች ገልፀዎል:: የአካባቢዉ ሙስሊም በሰልፍ ላይ ባለመገኘታቸዉ በአካባቢዉ የሚገኙ ሱቆችን በማዘጋት በግዳጅ በሰልፍ ላይ እንዲካፈሉ ማድረጋቸዉን ለማወቅ ተችሏል:: ይህ ሁሉ ከህዝብ ጋር ግብግብ ከመግጠም ጥያቄዎቻችንን መመለሱ አይቀልም???

No comments:

Post a Comment