Friday 17 August 2012

ድምፃችን ይሰማ


ዒድ ሙባረክ
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሳሊሀል አዕማል
ውድ ሙስሊሞች እየተፈፀመብን ያለው ግፍ፣ እየደረሰብን ያለው የመብት ረገጣና የህግ ጥሰት እንዲሁም ዲናችንን የሚያራክሱ ተግባራት በዚህ ታላቅ የዒድ በዓላችን በከተማችን የምንገኝ ከ1 ሚሊዮን የምንልቅ ሙስሊሞች አንድ በመሆን በዲናችን እንደማንደራደርና ዘብ እንደምንቆም በተግባር እንድናሳያቸው አስገድዶናል፡፡ በመሆኑም በዚህ ታላቅ የሙስሊሞች ቀን ስግደታችንን ፈፅመን ከፍተኛ የተቃውሞ ድምፅ በሰላማዊ መንገድ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ እናሰማለን!! ህዝብ ነንና ማንም ሊነፍገን የማይችለው ተቃውሞን የማሰማት ሙሉ መብት አለን፡፡ ስለዚህ ጥያቄያችን እንዲመለስ ኮሚቴዎቻችን እና የታሰሩት ሁሉ እንዲፈቱ እንጠይቃለን!! ውድ ሙስሊሞች የተቃውሞው ይዘት ከወትሮው የሚለየው ጥያቄዎቻችን የሚሊዮኖች መሆናቸውንና ወኪሎቻችን የሁላችንም መሆናቸውን ዳግም በአደባባይ ለመመስከር ሲሆን በተዛባ መረጃም ይሁን መረጃን ካለማግኘት የትግላችንን ሂደት ላልተረዱ ሁሉ ሰላማዊነታችንን በተግባር በማሳየት መንግስትም ህዝብንና ሃገርን የሚጠቅም ፍትሃዊ ምላሽ እንዲሰጠን ለመጠየቅ ነው፡፡ የተቃውሞ ሂደቱ ከዚህ እንደሚከተው ብቻ ይሆናል፡

ከሰላት በፊት የሚኖር ተቃውሞ


1ኛ. ሁላችንም በጧት 1 ሰዓት ላይ እስታዲየም እንገኛለን፡፡ በግዜ ሰግደው እኛን ለመሸወድ ስላሰቡ፡፡ ሆኖም ግን አስቀድመዎ ሰላት የሚጀመር ከሆነ ሰላቱን ሰግደን ቀሪ ወንድሞችና እህቶች እስኪመጡ እንጠብቃለን፡፡
2ኛ. በዲናችን ላይ ሲቀልዱና ህልውናችንን ሲሸጡ የከረሙ እስከ ዛሬ ስንቃወማቸው የነበሩ የመጅሊስ አመራሮችም ይሁኑ የመጅሊስ ዑለማ ም/ቤት አባላት እፊታችን ቆመው ንግግር ለማድረግ ከሞከሩ መዳፋችንን ጆሮዋችን ላይ በማድረግ ‹‹አሸዕብ ዩሪድ ኢስቃጠል መጅሊስ›› የሚል መፈክር በማሰተጋባት እናስቆማቸዋለን፡፡ ከመድረክ እንዲወርዱ እናደርጋለን፡፡
3ኛ. መድረክ መሪው አንዲት እኛ ክቡር ሙስሊሞችን የሚያጣጥልና የሚወርፍ ቃል ከተነፈሰ በተክቢራ እናስቆመዋለን፡፡
4ኛ. የመንግስት ባለስልጣን ተጋባዥ እንግዳ ካለ በእስር እና በእንግልት ላይ መሆናችንን በመቃወም ጆሮዎቻችንን በመዳፎቻችን በመያዝ ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› መፈክር በማሰማት እንቃወማለን፡፡

ከሰላት ቡኋላ የምናደርገው ተቃውሞ

1ኛ. ሰላት እንደተሰላመተ ሳንንቀሳቀስ ባለንቦት ቦታ ላይ ቆመን ለ8 ደቂቃ ነጭ ሶፍት/መሃረብ/ወረቀት ማውለብለብ፡፡ ሰላማዊነታችንን ለማሳየት፡፡
2ኛ. ባለንበት ቦታ ላይ ተንበርክከን ለ5 ቀቂቃ እጃችንን በካቴና ምልክት እንታሰራለን፡፡ ታስረናል! ታፍነናል! የታሰሩት ሁሉ ይፈቱልን ለማለት፡፡
3ኛ. ባለንበት ቦታ ቆመን 5 ደቂቃ እጅለ ለእጅ ተያይዘን ተክቢራ እናሰማለን!!
4ኛ. ባለንበት ቦታ ቆመን 5 ደቂቃ ጥያቄያችን ይመለስ!! እንላለን፡፡
4ኛ. ባለንበት ቦታ ቆመን 5 ደቂቃ ኮሚቴው ይፈታ!! እንላለን፡፡

5ኛ. ባለንበት ቦታ ቆመን 5 ደቂቃ የታሰሩት ይፈቱ!! እንላለን፡፡
6ኛ. ባለንበት ቦታ ቆመን 5 ደቂቃ ምርጫችን በመስጂዳችን!! እንላለን፡፡
7ኛ. ባለንበት ቦታ ቆመን 5 ደቂቃ ድምፃችን ይሰማ!! እንላለን፡፡
8ኛ. 10 ግዜ አቋማችን!! - አቋማችን!! እንላለን፡፡
9ኛ. 10 ግዜ ኮሚቴው ሳይፈታ - ምርጫ አንሳተፍም!! እንላለን፡፡
10ኛ. 10 ግዜ በእምነታችን - ጣልቃ አትግቡ!! እንላለን፡፡
11ኛ. 10 ግዜ ሀስቡን አላህ - ወኒዕመል ወኪል!! እንልና እንጨርሳለን፡፡ ከዚህ ቡኋላ ወደየመጣንበት እንመለሳለን፡፡
ሊፈጠሩ የሚችሉ ክስተቶች!

1ኛ. መንግስትና መጅሊስ የሚያደራጇቸው ቡድኖች እኛን ወደ ሁከት ለመቀስቀስ ቢጥሩ እንደከዚህ ቀደሙ በምንም መልኩ ምላሽ ባለመስጠት እናከሽፍባቸዋለን፡፡
2ኛ. በማንኛውም ቦታ በሴቱም በወንዱም በኩል ግርግር ቢፈጥሩ በምንም ዓይነት አንሮጥም ባለንበት ቦታ ቆመን እጅ ለእጅ ተያይዘን ግርግራቸውን እናከሽፋለን፡፡
3ኛ. መሃላችን ገብተው ህዝቡን ሰልፍ እናድርግ ብለው የሚቀሰቅሱ ካሉ እናጋልጣቸዋለን፡፡
4ኛ. ዝናብ ቢኖር ከዚህ በፊት እንዳሳየነው ሁሉ ፀንተን ድምፃችንን ከማሰማት አይገድብንም፡፡
ማስታወሻ፡ ምንም እንኳን ከሰላት በፊት ያሉ የአምልኮ ተግባራትን መተግበር ብንፈልግም ነገር ግን ሰላማዊ ተቃውሟችንን ሆን ብለው ለማደፍረስ የሰላት ሰአቱን ከተለመደው 2፡30 ቢያዘገዩት ‹‹ተክቢራ ›› ፤ ‹‹ሰላቱ ይጀመር›› እና ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› በማለት ተቃውሞ እናሰማለን፡፡
ውድ ሙስሊሞች ከላይ የተቀመጠውን የተቃውሞ ሂደት ብቻ ሙሉ በሙሉ በመተግበር ቁጣችንን እንገልፃለን፡፡ እንቃወማለን፡፡ እንኳንስ እንደዚህ ዓይነት ትልቅ መብት ተጥሶ አይደለም በማንኛውም ጉዳይ ላይ ዜጎች በሰላማዊ መንገድ የመቃወም መብት አላቸው፡፡ በመሆኑም በዲናችን ላይ እየተደረገ ያለውን የእጅ ጥምዘዛ፤ እየተባለ ያለውን እኔ የፈለኩትን ነገር ብቻ በግድ ተቀበል፤ በኮሚቴዎቻችን በዱዓቶች በወንድምና በእህቶች ላይ የተፈፀመውን እስራትና እየተፈፀመ ያለውን የህግ ጥሰት አጥብቀን እንቃወማለን!! ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱልን!! በዚህ አንድነታችንን አናሳያቸዋለን!! እኛ ሚሊዮኖች መሆናችንን በተግባር እናረጋግጥላቸዋለን፡፡ ዲናችንን ለድርድር እንደማናቀርብ በብረቱ ዓይናቸው አንዲመለከቱ እናደርጋለን!! በኛ ስም ለሚነግዱ አኼራን ዘንግተው ዲናቸውን በሽራፊ ሳንቲምና ስልጣን ለሸጡና ለሚሸጡ የመጅሊስ ግለሰቦች ካሁን ቡኋላ ምንም ዓይነት በር እንደማንከፍትና ለዚህ ክህደታቸው በህግ ተገቢውን የፍርድ ቅጣት እስኪያገኙ እንደምንታገል በአፅንኦት እናስገነዝባቸዋለን፡፡
ይህን ታላቅ የረመዳን ወር ክብር ሳይጠብቁ ለበደሉን አካላት በዒድ በዓላችን ደስታችን ለማደብዘዝ ለቋመጡትም ሁሉ አላህ የእጃቸውን አንዲከፍላቸው እንማፀነዋለን፡፡ የነርሱ ሀሳብ መቼም ቢሆን እንደማይሳካላቸው አስምረን እንነግራቸዋለን፡፡ መብቱን ለጠየቀ ህዝብ ምላሽ መስጠት ክብር ነው፤ ህገ መንግስቱ ይከበር ላለ ህዝብ ጥያቄዉን በአግባቡ መመለስ ታላቅነት ነው፤ ሰላማዊ የመብት ትግልን አማራጩ ያደረገን ህዝብ ማዳመጥ ብልህነት ነው፤ በተገላቢጦሽ መሆን ግን ተቃራኒውን መሆን ነው፡፡ እናም አሁንም ጥያቄዎቻችን ይመለሱ!!! ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ!!! አላሁ አክበር!!! አላህ ታላቅ ነው!!! በተለያዩ አማራጮች ለወዳጅ ዘመዶቾ መልዕክቱን ያስተላልፉ

No comments:

Post a Comment